ሩሲያን የመነጠል ሙከራዎች መክሸፋና ከአፍሪካ ጋር የተጠናከረው ሁለንተናዊ ግንኙነት

January 22
1 hr

Episode Description

"በዩክሬን ውስጥ ምን እየሆነ እንዳለ [አሜሪካኖቹ] ሙሉ በሙሉ እንደሚረዱ እርግጠኛ ነኝ። ምዕራባውያን በተለይም አውሮፓውያን የሞራል ኪሳራ እንዲሁም በወታደራዊ አቅርቦት እና ቴክኖሎጂ አቅማቸው ላይ በዩክሬን ከፍተኛ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ተረድተዋል። የትራምፕ አስተዳደርም በዩክሬን ውስጥ ማን የበላይ እንደሆነ በትክክል ያውቃል። ስለዚህ ስለ ሰላማዊ መፍትሄ በቁም ነገር ማሰባቸው ተገቢ ነው።" ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት በጥር 20፣ 2026 (እ.ኤ.አ) የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ 2025 ዲፕሎማሲያዊ ግምገማ እና ለ2026 የተያዘውን ውጥን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ዳዊት መዝገበ ምልከታቸውን ያጋሩናል። በሁለተኛው ክፍል የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የአህጉሪቱን የግብርና ዘርፍ ለማበልፀግ ስለተነደፈ እቅድ እንዳስሳለን። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ማንደፍሮን (ዶ/ር) አነጋግረናል።

በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

See all episodes