Episode Description
"ጤነኛ አእምሮ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚያ የአውሮፓውያን ዲፕሎማሲ ውስጥ እንዳይዘፈቅ። እንዳትዘፈቁ! ምክንያቱም አባቶቻችን በምኒልክ ዘመን ያለ ጫማ፣ ያለ ሱፍ ልብስ፣ ያለ ከረባት የአውሮፓውያንን፣ የምዕራብ አውሮፓውያንን ተንኮል ማየት ይችሉ ነበር። እኛ ግን በዚህ ሁሉ ዲግሪ፣ በዚህ ሁሉ ሱፍ እና ዘመናዊ መኪና እነዚህ ሰዎች የሰለጠኑ ስለሚመስሉን ተንኮላቸውን ማየት ተስኖናል። አይደለም፣ እነሱ አረመኔዎች ናቸው። እውነቱን እንጋፈጠው፤ ይህ አረመኔነት ነው።" ሲሉ የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ፣ ደራሲ እንዲሁም የቱሪዝም ባለሙያ እና የባህል ጉዳዮች አንቂ ራስ ዐቢይ ጥላሁን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የዓድዋን ድል ትርጉም ከወቅታዊው የአፍሪካ ሉዓላዊነት ትግል ጋር በማገናኘት፤ የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ፣ ደራሲ እንዲሁም የቱሪዝም ባለሙያ እና የባህል ጉዳዮች አንቂ ራስ ዐቢይ ጥላሁን ጋር በጥልቀት እንወያያለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡