Episode Description
"የዝግጅቶች የጉባኤ ወይም MICE ቱሪዝም በመባል የሚታወቀው ዘርፍ በ180 ሀገራት ውስጥ በተደረጉ የተለያዩ ስብሰባዎች ወደ 1.6 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን አዘዋውሯል፤ 1.3 ትሪሊዮን ዶላር ገቢም አስገኝቷል። ስለዚህ በቢሊዮኖች ሳይሆን በትሪሊዮኖች የሚቆጠር ነው። ይህም በቀጥታ ሽያጭ ብቻ የሚገኝ ነው። ከእሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሌሎች ኢንዱስትሪዎች ሲጨምር ወደ 3.1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የንግድ ሽያጭ ይደርሳል። ይህም በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ሲሰላ 1.8 ትሪሊዮን ዶላር አካባቢ ነው። በእርግጥ ይህ ኢንዱስትሪ ራሱ በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ ኢኮኖሚዎች አንዱ ያደርገዋል። ስለዚህ ከአንድ ሀገር ኢኮኖሚ አንፃር ስንየው፣ በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ ኢኮኖሚዎች 16ኛ ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው እገምታለሁ።" ሲሉ ዮአዳን ጥላሁን፣ የ«ፍሎውለስ ኢቨንትስ» መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ዝግጅቶችና ኤግዚቢሽን አዘጋጆች ማህበር የቀድሞ ፕሬዚዳንት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት» ዝግጅታችን፣ የዝግጅቶችና ስብሰባዎች ኢንዱስትሪ ለዓለምና ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ያለውን ግዙፍ ፋይዳ፣ እንዲሁም ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ያለውን ስትራቴጂያዊ ሚና እንቃኛለን። በሁለተኛው ክፍላችን ደግሞ፣ ከኢኮኖሚ ትስስርና ከአህጉራዊ ትብብር አንፃር የአፍሪካ ወደብ አልባ ሀገራት የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶችና ዕድሎች ከፖሊሲ አማካሪ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር)ጋር እንዳስሳለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበዉን ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡