Episode Description
አፍሪካ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነው የአህጉሪቱ ህዝብ ከ25 ዓመት በታች ነው። ይህ ግዙፍ የሰው ኃይል ወደ ኢኮኖሚያዊ ውጤት እንዲቀየር፣ ትምህርት እና ሥልጠና ከኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር መጣጣም አለባቸው።
"ኢትዮጵያ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናት። ከ70 በመቶ በላይ የሆነው ህዝባችን ከ30 ዓመት በታች ነው። መንግስት ለስራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ ኢላማ በማስቀመጥ ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል። ይህንን ለማሳካትም በ2020 መጀመሪያ ላይ የተቋቋመውና በአሁኑ ወቅት ወጣት ከሚባሉ ተቋማት አንዱ የሆነው 'የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር' ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው።" ሲሉ በኢትዮጵያ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ብሔራዊ አስተባባሪ እና የ ‘አሶሴሽን ኦፍ ቻርተርድ ሰርቲፋይድ አካውንታንትስ’ (ACCA) ባልደረባ ቃልኪዳን ታደሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ የራሷን የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ለማፍራት የምታደርገውን ጥረት እና ስለ "ክህሎት ሉዓላዊነት" እንወያያለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡