የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ነፃ ንግድ ቀጣና ፡- ኢትዮጵያ የአፍሪካ እድገትና ሉዓላዊነት ማዕከል የመሆን ውጥን

January 22
1 hr

Episode Description

ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ምርቶች ለማንቀሳቀስ ስታቅድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ የአፍሪካን የአቪዬሽን ታሪክ የሚቀይር ግዙፍ የኤርፖርት ፕሮጀክት ጀምሯል። እነዚህ የአየር እና የየብስ መሰረተ ልማቶች ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና ለአፍሪካ ትስስር ያላቸው ፋይዳ ወሳኝ ነው፣የኢኮኖሚ ዞኖችም ቁልፍ ሚናን ይጫወታሉ።

"ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር ማዕከላዊ ሚና መጫወት አለባት። ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ኢትዮጵያን የአፍሪካ ማኑፋክቸሪንግ እና የሎጂስቲክስ ማዕከል እንድትሆን ይረዱናል።[...] የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነትን በመጠቀም ያለንን አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት መቀየር አለብን።" ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው ዝግጅታችን፣የኢትዮጵያን የኢንደስትሪ ልማትና ከአህጉራዊ የነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት ተጠቃሚነት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር) ጋር እንመለከታለን። አዲሱ የኤርፖርት ፕሮጀክት ለአፍሪካ አቪዬሽን ያለውን ፋይዳም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ያስተላለፉትን መልእክት እንቃኛለን።

በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

See all episodes

Never lose your place, on any device

Create a free account to sync, back up, and get personal recommendations.