የኢትዮጵያ የቅመማ ቅመም ምርት አዲስ መልክ

Dec 18, 2025
1 hr

Episode Description

የኢትዮጵያ የቅመማ ቅመም ዘርፍ ባለው ከፍተኛ እምቅ አቅም ልክ ተገቢውን ዋጋ አላገኘም። በሌላ በኩል ደግሞ አፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማስፈን በደቡብ-ደቡብ ትብብር እና በሩሲያ-አፍሪካ ትብብር ላይ እየሰራች ነው።

የጓሮ እርሻዎች ተባባሪ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቅድስት አምዴ "እኛ ጋር ወደ 23 የሚደርሱ የምግብ ቅመሞች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹን እናውቃቸዋለን፤ አንዳንዶቹን አናውቃቸውም። ወደ 800 የሚጠጉ የመድኃኒት ዕፅዋትም አሉን። ይህ በጣም ሰፊ የልዩ ልዩ ዝርያዎች ሀብት ነው። በየቦታው አይገኝም። ስለዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ዕድል አለ ብዬ አስባለሁ።" ስትል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች፡፡

በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የጉዋሮ ማይክሮ-ፋብሪካዎች የአርሶ አደሩን ገቢ እና የሀገርን የግብርና ዘርፍ መዋቅር እንዴት እየቀየሩ ነው? የሚለውን እንመለከታለን። ለዚህም የጓሮ እርሻዎች ተባባሪ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቅደስት አምዴን ጋብዘናል። እንዲሁም፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ዲን ዘሪሁን ደምረው (ዶ/ር) እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች አፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነትን በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስና በትብብር እንዴት ታረጋግጣለች? በሚለው ዙሪያ ያደረጉትን ውይይት እንፈትሻለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

See all episodes

Never lose your place, on any device

Create a free account to sync, back up, and get personal recommendations.