Episode Description
አፍሪካ ትልቅ ወጣት ህዝብን ይዛለች፤ ነገር ግን ይህ የዴሞግራፊ ዕድል ወደ እውነተኛ የኢኮኖሚ ውጤት እንዲቀየር የፋይናንስ ተደራሽነት እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች ወሳኝ ናቸው።
"የውስጥ ሀብታችንን የምንጠቀምበት መንገድ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ያለንን ጥገኝነት ለመቀነስ ይረዳናል። ማናቸውም ሀገር ያለ ዓለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ ብቻውን ኢኮኖሚውን ማሳደግ ይችላል ማለቴ አይደለም፤ ድጋፋቸው ያስፈልገናል። ነገር ግን ማድረግ ያለብን ጥገኝነታችንን መቀነስ ነው። የውጭ ተቋማትን አስተዋጽኦ ለመቀነስ ማዕድናችንን ማቀነባበር አለብን። ለምሳሌ በማሊ ከወርቅ ብቻ ብዙ ወጣቶችን ስራ ማስያዝ እና ዓላማዎቻችንን ማሳካት እንችላለን።" — ሲሉ ዣን ፑዲዩጎ፣ የቪዥን ፈንድ ማሊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የመንግስት የወጣቶች ልማት እና ድህነት ቅነሳ አማካሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ በሳህል ቀጣና በተለይም የማሊ ወጣቶች የኢኮኖሚ ማካተት እና በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ መስፋፋት ዙሪያ የሚደረጉ ወሳኝ ውይይቶችን እንቃኛለን። ለዚህም የቪዥን ፈንድ ማሊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የመንግስት አማካሪ ዣን ፑዲዩጎ እንዲሁም ዮናስ ፍቅሩ፣ የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር ቆይታ አድርገናል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡