ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ቀጠናዊ የዋጋ ሰንሰለት፡ አፍሪካ ሀብቷን ውስጣዊ አቅም እንዴት ማቆየት ትችላለች?

July 30
1 hr

Episode Description

አፍሪካ ለዓለም ገበያ በርካታ ጥሬ ዕቃዎችን የምታቀርብ ቢሆንም፣ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶችም ጥገኛ ናት። አሁን ላይ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ሲመሠረት፣ ትኩረቱ ወደ ቀጠናዊ የዋጋ ሰንሰለቶች ግንባታ እና የሎጂስቲክስ አውታሮችን በማጠናከር ሀብቱ በአህጉሪቱ እንዲቆይ ማድረግ ላይ እየተሸጋገረ ይገኛል።

" አብዛኛዎቹ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ከአፍሪካ አይደሉም፤ ከ90 እስከ 95 በመቶ የሚሆነው የገቢና የወጪ ንግድ ጭነት የሚከናወነው በአውሮፓ ወይም በአሜሪካ ኩባንያዎች ነው። ይህ በወጪያችን ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በቁጥር ላሳያችሁ፤ ከቻይና ሻንጋይ እስከ ኢትዮጵያ ለአንድ የዕቃ መጫኛ ኮንቴነር የምንከፍለውን ክፍያ እንመልከት..."  ሲሉ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሎጅስቲክስ እና ዕሴት ሰንሰለት ትምህርት ክፍል ኃላፊ መሳይ አየለ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ 

በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ የንግድና የሎጂስቲክስ አውታሮቿን በማቀናጀት ከጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት ወጥታ የራሷን የዋጋ ሰንሰለት እንዴት መዘርጋት እንዳለባት እንቃኛለን።

 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡



See all episodes