ኃይል፣ ወደብ እና ቅርስ፡- የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ እና የሉዓላዊነት ትግል

January 2
1 hr

Episode Description

የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ቀጠና በጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ናቸው። እስራኤል ለሶማሌላንድ የሰጠችው ዕውቅና፣ የሁቲ አማጽያን ዛቻ እና ከእስራኤል ጋር የገብበት ፍጥጫ ቀጥሏል፡፡ በሌላ በኩል፣ ከመቅደላ የተዘረፉ ቅርሶቻችንን ከብሪታኒያ ሙዚየም "በብድር" ሳይሆን በክብር የመመለስ ትግል የአፍሪካዊያን ሌላ ሜዳ ሆኗል።

"እስራኤል ለሶማሌላንድ ስትራቴጂካዊ ቦታ እና አስፈላጊነት ትኩረት እየሰጠች ነው፤ ምክንያቱም ሁቲዎች በእስራኤል ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ኢላማዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው። ስለዚህ ይህ አንዱ ጉዳይ ነው።" ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት መሰናዶ የሶማሌላንድ የሀገርነት እውቅናና ትርጓሜውን ከፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ጋር እንፈትሻለን። ተዘርፈው ለእይታ የሚቀርቡበት የብሪታኒያ ሙዚየም ቅርሶችን "በውሰት" ለአፍሪካ ሀገራት የመስጠት እቅድና የተዘረፉ ቅርሶችን የማስመለስ ሂደት የትግል መልክን በተመለከተም ከቅርስ አስተዳደር እና ጥበቃ ከፍተኛ ተመራማሪ ተስፋዬ አራጌ ጋር እንወያያለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

See all episodes

Never lose your place, on any device

Create a free account to sync, back up, and get personal recommendations.